በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
መሳፍንት 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፥ “እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፤ ዛሬ ግን እባክህ አድነን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም እግዚአብሔርን፣ “ኀጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንም ጌታን፥ “ኃጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ግን እግዚአብሔርን “በእርግጥ በድለናል፤ አንተ በእኛ ላይ የፈለግኸውን አድርግብን፤ ብቻ እባክህ የዛሬን አድነን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፦ እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፥ አንተ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፥ ዛሬ ግን፥ እባክህ፥ አድነን አሉት። |
በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
ዳዊትም ናታንን፥ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው። ናታንም ዳዊትን አለው፥ “እግዚአብሔር ደግሞ ኀጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትምም።
ሕዝቡንም ከቈጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው፤ ዳዊትም እግዚአብሔርን፥ “ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኀጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።
ዳዊትም ጋድን፥ “በሁሉም እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ በሰው እጅ ከምወድቅ ይልቅ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል” አለው።
እነርሱም፦ እግዚአብሔርን ትተን በዓሊምንና ምስሎቹን በማምለካችን በድለናል፤ አሁንም ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፤ እናመልክሃለንም” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ ።
ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፤ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።
እነርሱም ወደ መሴፋ ተሰበሰቡ፤ ውኃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት በምድር ላይ አፈሰሱ፤ በዚያም ቀን ጾሙ፤ በዚያም፥ “በእግዚአብሔር ፊት በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በእስራኤል ልጆች ላይ በመሴፋ ፈረደ።