መሳፍንት 1:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞሬዎናውያንም ድብና ቀበሮዎች በሚኖሩበት በመርስኖኖስ ተራራ መቀመጥ ጀመሩ፤ ነገር ግን የዮሴፍ ወገን እጅ በአሞሬዎናውያን ላይ ጸናች፤ ገባርም አደረጉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞራውያንም በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎንና በሻዓልቢም ኑሯቸውን ቀጠሉ፤ ይሁን እንጂ የዮሴፍ ወገን በበረታ ጊዜ ተገድደው የጕልበት ሥራ ከመሥራት አላመለጡም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞራውያን በሔሬስ ተራራና በኤሎን በሸዓልቢምም በመቀመጥ ጸኑ፥ ነገር ግን የዮሴፍ ቤት እጅ ከበደች፥ አስገበረቻቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሞራውያን በሔሬስ ተራራና በአያሎን፥ በሻዓልቢም መኖርን ቀጠሉ፤ ነገር ግን የዮሴፍ ልጆች (የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች) የእነርሱ ተገዢዎች አድርገው የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞራውያን በሔሬስ ተራራና በኤሎን በሸዓልቢምም በመቀመጥ ጸኑ፥ ነገር ግን የዮሴፍ ቤት እጅ ከበደች፥ አስገበረቻቸውም። |
የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
ያን ጊዜም እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆች እጅ አሞሬዎናውያንን አሳልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገባዖን እነርሱን ባጠፋበት፥ እነርሱም ከእስራኤል ልጆች ፊት በጠፉበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እንዲህም አለ፥ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”
አሞሬዎናውያንም የዳንን ልጆች በተራራማው ሀገር አስጨነቁአቸው፤ ወደ ሸለቆው እንዲወርዱ አይፈቅዱላቸውም ነበርና።