ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር።
መሳፍንት 1:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬምም በጋዜር የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው በጋዜር ተቀመጡ፤ ገባሮችም ሆኑላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም የኤፍሬም ወገኖች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ማስወጣት አልቻሉም፤ ስለዚህ ከነዓናውያን በመካከላቸው እዚያው መኖርን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዚሁም የኤፍሬም ወገኖች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ማስወጣት አልቻሉም፤ ስለዚህ ከነዓናውያን በመካከላቸው እዚያው መኖርን ቀጠሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤፍሬም ነገድም በጌዜር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን አላባረሩም ነበር፤ ስለዚህ ከነዓናውያን እዚያው ከእነርሱ ጋር ኗሪዎች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬምም በጌዝር የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላወጣቸውም፥ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው በጌዝር ተቀመጡ። |
ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር።
የግብፅም ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጋዜርን ያዘ፤ በእሳትም አቃጠላት፤ በሜርጎብ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንንም ገደላቸው፤ ለልጁም ለሰሎሞን ሚስት እነዚያን አገሮች ትሎት አድርጎ ሰጥቶአት ነበር።
በዚያ ጊዜም የጋዜር ንጉሥ ኤላም ላኪስን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር በሰይፍ ስለት እርሱንና ሕዝቡን መታ፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም።
በጋዜርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን ኤፍሬም አላጠፋቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ ገባርም ሆኑ።
ዛብሎንም በቄድሮንና በአማን የሚኖሩትን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፤ ግብርም የሚገብሩላቸው ሆኑ።