መሳፍንት 1:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም በበረቱ ጊዜ ከነዓናውያንን ገባሮች አደረጉአቸው፤ ነገር ግን ፈጽመው አላጠፏቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ፈጽሞ አላስወጧቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ፈጽሞ አላስወጧቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ብርታት ባገኙ ጊዜ ከነዓናውያን ለእነርሱ የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር፤ ሆኖም ሁሉንም አላስወጡም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም በበረቱ ጊዜ ከነዓናውያንን አስገበሩአቸው፥ ፈጽመውም አላወጡአቸውም። |
የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
ምናሴም የሰቂቶን ከተማ ቤትሶንንና መንደሮችዋን መሰማሪያዎችዋንም፥ ኢቀጸአድንና መንደሮችዋን፥ የዶርን ነዋሪዎችና መንደሮችዋን፥ የዮበለዓምን ነዋሪዎች፥ መሰማሪያዎችዋንና መንደሮችዋን፥ የመጊዶን ነዋሪዎች መሰማሪያዎችዋንና መንደሮችዋን አልወረሳቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያች ሀገር ይቀመጡ ዘንድ ጸኑ።
ኤፍሬምም በጋዜር የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው በጋዜር ተቀመጡ፤ ገባሮችም ሆኑላቸው።
ሳኦልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ እህል አልቀመሱም። ሀገሩም ሁሉ ምሳ አልበላም።