ዳዊትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፤ ሲወጣም ያለቅስ ነበር፤ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፤ ያለጫማም ይሄድ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው ነበር፤ እያለቀሱም ይወጡ ነበር።
ኢዮብ 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኃጥኣን እጅ ተሰጥተዋልና፤ የምድር ፈራጆችን ፊት ይሸፍናል፤ እርሱ ካልሆነ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣ እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤ ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፥ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፥ ይህንን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ሌላ ማን ነው?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር በክፉ ሰዎች እጅ ተላልፋ ስትሰጥ እርሱ የዳኞችን ዐይን ይሸፍናል፤ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ካልሆነ ታዲያ፥ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፥ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፥ እርሱ ካልሆነ ማን ነው? |
ዳዊትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፤ ሲወጣም ያለቅስ ነበር፤ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፤ ያለጫማም ይሄድ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው ነበር፤ እያለቀሱም ይወጡ ነበር።
ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኀይል ነበረ። እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፣ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።