ኢዮብ 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጽድቅ ብጠራው፥ ባይሰማኝም፥ የእርሱን ፍርድ እለምናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቅ ብሆንም እንኳ፣ ልመልስለት አልችልም፤ ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ላደርግ የምችለው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ብሆንም እንኳን ልመልስለት አልችልም፥ ፈራጄን እማጸናለሁ እንጂ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ ሆኜ ብገኝ እንኳ፥ ፈራጁ አምላክ እንዲምረኝ እለምነዋለሁ እንጂ መልስ ልሰጠው አልደፍርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻድቅ ብሆን ኖሮ አልመልስለትም ነበር፥ ወደ ፈራጄም እለምን ነበር። |
እያለቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስሄዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።”