ኢዮብ 6:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እናንተ ያለ ምሕረት መጣችሁ፤ ቍስሌንም አይታችሁ ፈራችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እናንተ እንደዚያ ሆናችሁብኝ፤ መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እናንተ እንደዚሁ ሆናችኋል፥ መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም ለእኔ እንደ እነዚያ ደረቅ ወንዞች ናቸሁ። የደረሰብኝን መከራ አይታችሁ ወደ ኋላ አፈገፈጋችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እናንተ እንደዚሁ ሆናችኋል፥ መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ። |
በተግሣጽህ ስለ ኀጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ ሰውነቱንም እንደ ሸረሪት አቀለጥኻት፤ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከንቱ ይታወካሉ።
ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥ ከወንድምነቱ የራቀ ነው። በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች። ብልህ ሰውም ያገኛታል። ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም።
ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ከዋክብትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንተዋት፤ ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንሂድ።