የመጀመሪያይቱን ስም ዕለት፥ የሁለተኛይቱንም ስም ቃስያ፥ የሦስተኛይቱንም ስም አማልትያስቂራስ ብሎ ሰየማቸው።
ኢዮብ 42:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰማይ በታች እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች ያሉ የተዋቡ ሴቶች በሀገሩ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች የተዋቡ ሴቶች በምድሪቱ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋራ ርስት ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆችም ያሉ የተዋቡ ሴቶች በአገሩ ሁሉ አልተገኙም፥ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓለም ላይ የኢዮብን ሴቶች ልጆች በቊንጅና የሚወዳደሩአቸው ሴቶች አልነበሩም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት አካፈላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆችም ያሉ የተዋቡ ሴቶች በአገሩ ሁሉ አልተገኙም፥ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው። |
የመጀመሪያይቱን ስም ዕለት፥ የሁለተኛይቱንም ስም ቃስያ፥ የሦስተኛይቱንም ስም አማልትያስቂራስ ብሎ ሰየማቸው።
ኢዮብም ከደዌው ከዳነ በኋላ መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ ኢዮብም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሁለት መቶ አርባ ነው። ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
“የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ ስጥ።
ከየነገዳችሁ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎችን አምጡ፥ ተነሥተውም ሀገሪቱን ይዙሩአት፤ ለመክፈልም እንዲያመች ገልጠው ይጻፉአት፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።