ኢዮብ 39:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ ከጥበብህ የተነሣ ጭልፊት ያንዣብባልን? ወይስ ክንፎቹን ወደ ደቡብ ይዘረጋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጭልፊት የሚበርረው፣ ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው፣ በአንተ ጥበብ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ጭልፊት የሚያንዣብበው፥ ክንፎቹንስ ወደ ደቡብ የሚዘረጋው በአንተ ጥበብ ነውን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውኑ ጭልፊት የሚያንዣብበው፥ ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው በአንተ ጥበብ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ከጥበብህ የተነሣ ጭልፊት ያንዣብባልን? ወይስ ክንፎቹን ወደ ደቡብ ይዘረጋልን? |
ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ፥ ዋሊያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
“አሮንም ስለ ራሱ ኀጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ወይፈኑን ያቀርባል፤ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል፤ ስለ ኀጢአቱ የእርሱን መሥዋዕት ወይፈኑን ያርዳል።