ኢዮብ 39:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍጣውም መሬትን ያጠፋል፤ የመለከትም ድምፅ እስከሚሰማው አያምንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወኔ መሬቱን እየጐደፈረ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነውጥና በቁጣ መሬትን ይውጣል፥ የመለከትም ድምፅ ቢሰማ አይቆምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እምቢልታው ሲነፋ ሲቃ ይዞአቸው በጭካኔና በቊጣ ወደ ጦር ሜዳ ይሸመጥጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጭካኔና በቍጣ መሬትን ይውጣል፥ የመለከትም ድምፅ ቢሰማ አይቆምም። |
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፤ ነፍሴም አእምሮዋን አጥታለች፤ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴም የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምታለችና ዝም እል ዘንድ አልችልም።
አደመጥሁ፤ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ ማናቸውም፦ ምን አድርጌአለሁ? ብሎ ከክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ የሚሮጠውም ወደ ሰልፍ እንደሚሮጥ ፈረስ ሲሮጥ ደከመ።
ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን?