ኢዮብ 39:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኮቴው በሸለቆው ውስጥ ይጐደፍራል፥ በጕልበቱም ወደ ሜዳ ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጕልበቱ እየተመካ በብርቱ ይጐደፍራል፤ ጦርነት ሊገጥም ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸለቆው ውስጥ በኮቴው ይጐደፍራል፥ በጉልበቱም ደስ ይለዋል፥ ሰይፍ የታጠቁትንም ለመጋፈጥ ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሶቹ ወደ ጦር ሜዳ ተጋልበው ሲሄዱ በጒልበታቸው በመመካት ሶምሶማ ይረግጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኮቴው በሸለቆው ውስጥ ይጐደፍራል፥ በጉልበቱም ደስ ይለዋል፥ ሰይፍም የታጠቁትን ለመገናኘት ይወጣል። |
በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በእግዚአብሔር በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።
አደመጥሁ፤ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ ማናቸውም፦ ምን አድርጌአለሁ? ብሎ ከክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ የሚሮጠውም ወደ ሰልፍ እንደሚሮጥ ፈረስ ሲሮጥ ደከመ።