እግር ይሰብረው ዘንድ፥ የምድረ በዳም አውሬ ይረግጠው ዘንድ ትረሳለች።
እግር እንደሚሰብረው፤ የዱር አውሬም እንደሚረግጠው አታስብም።
እግር ሊሰብረው እንደሚችል፥ የምድረ በዳም አውሬ ሊረግጠው እንደሚችል ትረሳለች።
‘በዚያ የሚያልፍ በእግሩ ይሰብረዋል፤ የዱር አውሬም ረግጦ ያደቀዋል’ ብላ አታስብም።
እግር ይሰብረው ዘንድ፥ የምድረ በዳም አውሬ ይረግጠው ዘንድ ትረሳለች።
ዕንቍላልን በመሬት ላይ ትጥላለች፥ በአፈርም ውስጥ ታሞቀዋለች፥
የእርስዋ እንዳልሆኑ በልጆችዋ ላይ ትጨክናለች፤ ያለ ፍርሀትም በከንቱ ትሠራለች፤