ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።
ኢዮብ 39:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰጎን ክንፍዋን በደስታ ታንቀሳቅሳለች፥ በፀነሰችም ጊዜ ልትበላ ትመኛለች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰጎን ክንፎቿን በደስታ ታራግባለች፤ ነገር ግን እንደ ሽመላ ላባዎች ሊሆኑ አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እንኳን እንደ ሸመላ ባትበርም፥ የሰጐን ክንፍ በደስታ ይንቀሳቀሳል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰጎን ክንፎችዋን በፍጥነት ትዘረጋለች፤ ነገር ግን እንደ ሸመላ አትበርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰጐን ክንፍ በደስታ ይንቀሳቀሳል፥ ነገር ግን ክንፉና ላባው ጭምተኛ ነውን? |
ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።
ለንጉሡም ከኪራም አገልጋዮች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር፥ የዝሆንም ጥርስና ዝንጀሮ ይዘው ይመጡ ነበር።
ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ፥ ዋሊያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፣ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፣ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።