አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም ያርፋሉ።
እንስሳት ይጠለላሉ፤ በየዋሻቸውም ይቈያሉ።
አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም ይቀመጣሉ።
በዚያን ጊዜ የዱር አውሬዎች ሸሽተው ወደየመሸሸጊያቸው ይገባሉ፤ በየዋሻቸውም ውስጥ ይሰወራሉ።
በዋሾቻቸው ውስጥ ተጋድመው በጫካም ውስጥ አድብተው ይቀመጣሉና።
የቤቱ ጌታም አደረገው፥ በገንዘቡ ሁሉ ላይ ገዢ አደረገው፥
አለቆቹን ሁሉ እንደ እርሱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም እንደ እርሱ ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።