የአዜብ ነፋስ በተኮሰ ጊዜ ያንተ ልብስህ የሞቀ ነው። እንግዲህ በምድር ላይ ፀጥ በል።
ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ባለች ጊዜ፣ ከሙቀት የተነሣ በልብስህ ውስጥ የምትዝለፈለፍ ሆይ፤
በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥ ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
ሰማዩ ነሐስ በመሰለ ጊዜ አንተ በኀይለኛው የበረሓ ነፋስ በሙቀት ትቀልጣለህ።
የደመናትን ክፍሎች፥ አስፈሪ የሆነውንም የኀጢአተኞችን አወዳደቅ ያውቃል።
እንደ ቀለጠ መስተዋት ብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?
“በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥ ወይስ ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን?
ወደ ሙቀት ሲቀርብ በቀለጠ ጊዜ ምን እንደ ነበረ አይታወቅም።
የአዜብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም ‘ድርቅ ይሆናል፤’ ትላላችሁ እንዲሁም ይሆናል።