ኢዮብ 37:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደመናትን ክፍሎች፥ አስፈሪ የሆነውንም የኀጢአተኞችን አወዳደቅ ያውቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን፣ የርሱን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ የደመናውን መንሳፈፍ፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናን በሕዋው ላይ የሚያንሳፍፈውንና ሁሉን የሚያውቀውን የአምላክን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ የደመናውን ሚዛን፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን? |
ኀያሉ እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅ አድርጎ ያንጐደጕዳል፤ ለእንስሳት በየጊዜው ምግባቸውን ያዘጋጃል፥ የሚተኙበትንም ጊዜ ያውቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይደንግጥብህ፤ ሥጋህም ልብህም ከግዘፉ አይለወጥብህ፤ እርሱም እኛ የማናውቀውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
እርሱ የምድርን ክበብ ያጸናል፤ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው፥ እንደ ድንኳንም ለመኖሪያ የሚዘረጋቸው፤