ኢዮብ 37:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤ ቁም፥ በእግዚአብሔርም ኀይል ተገሠጽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኢዮብ ሆይ፤ ይህን ስማ፤ ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! እስቲ ዝግ ብለህ አድምጥ፤ እግዚአብሔር የሚያደርጋቸውንም ድንቅ ሥራዎች ልብ ብለህ አስተውል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ። |
ኀያሉ እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅ አድርጎ ያንጐደጕዳል፤ ለእንስሳት በየጊዜው ምግባቸውን ያዘጋጃል፥ የሚተኙበትንም ጊዜ ያውቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይደንግጥብህ፤ ሥጋህም ልብህም ከግዘፉ አይለወጥብህ፤ እርሱም እኛ የማናውቀውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።