ኢዮብ 36:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በጥበብ ብርቱና ኀያል የሆነ እግዚአብሔር፥ የዋሁን ሰው እንደማይጥለው ዕወቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፥ እርሱም በጥበባዊ ኃይሉም ጽኑ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእርግጥ እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ማንንም አይንቅም፤ እርሱም ሁሉንም ነገር ያስተውላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፥ እርሱም በማስተዋል ብርታት ኃያል ነው። |
እግዚአብሔር በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰው ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።