ኢዮብ 36:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሌ ሐሰት ያይደለ እውነት ነው። አንተም የዐመፅ ቃላትን አትሰማም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሌ በእውነት ሐሰት የለበትም፥ በእውቀትም ፍጹም የሆነ ከአንተ ጋር አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግሬ ሐሰት ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን፤ ከአንተ ጋር የምነጋገረው እኔ የተሟላ ዕውቀት እንዳለኝ ዕወቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃሌ በእውነት ያለ ሐሰት ነው፥ በእውቀትም ፍጹም የሆነ ከአንተ ጋር አለ። |
የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው ተከትዬ፥ ሁሉንም በየተራው እውነተኛውን እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሁኖ ታየኝ።
ፊልክስ ግን አይሁድ ከጥንት ጀምሮ የክርስቲያንን ወገኖች ሕግና ትምህርት እንደሚቃወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለዚህም “እንኪያስ የሺ አለቃው ሉስዮስ በመጣ ጊዜ ነገራችሁን እናውቅ ዘንድ እንመረምራለን” ብሎ ቀጠራቸው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በአእምሮ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃናት ሁኑ፤ በዕውቀትም ፍጹማን ሁኑ።
የእግዚአብሔርን ቃል በሌላ ቀላቅለው እንደሚሸቅጡ እንደ ብዙዎች አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከ በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ እንናገራለን።
ከእናንተ ወገን የሚሆን ኤጳፍራስም ሰላም ይላችኋል፥ እርሱ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፤ እግዚአብሔር በሚወደው ነገር ሁሉ ምሉኣንና ፍጹማን እንድትሆኑ፥ ስለ እናንተ ዘወትር ይጸልያል፤ ይማልዳልም።