ኢዮብ 36:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ገና የምናገረው ነገር አለኝና ጥቂት ታገሠኝ፥ እኔም አስተምርሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በእግዚአብሔር ፈንታ ሆኜ የምለው አለኝ፤ ጥቂት ታገሠኝና እነግርሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ገና ስለ እግዚአብሔር የሚነገር አለኝና ጥቂት ቆየኝ፥ እኔም አስታውቅሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ስለ እግዚአብሔር የምናገረው ገና ሌላ ነገር ስላለ፥ እንዳብራራልህ ጥቂት ታገሠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገና ስለ እግዚአብሔር የሚነገር አለኝና ጥቂት ቆየኝ፥ እኔም አስታውቅሃለሁ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ፤ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።