ኢዮብ 35:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተ ተዋቅሰህ ምን ትላለህ? ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ የምትል አንተ ማን ነህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’ ማለትህ፣ ትክክል ይመስልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ይህ ትክክል ነው ብለህ ታስባለህን? ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነኝ ማለትህ ትክክል ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ጽድቅ እንደ ሆነ ታስባለህን? ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን? |
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።