ኢዮብ 34:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጽሞ ያልበደለ፥ ግፍን ከሚሠሩም ጋር ያልተባበረ፥ ከኃጥኣንም ጋር ያልሄደ፥ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ይተባበራል፤ ከኀጢአተኞችም ጋራ ግንባር ይፈጥራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጓደኞቹ ክፉ አድራጊዎች ናቸው፤ የሚውለውም ከክፉ አድራጊዎች ጋር ነው። |
እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም።
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፥ እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅደሱም አገለግል ዘንድ።