ኢዮብ 34:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ የሚለው፥ መኳንንቱንም፦ ክፉዎች ናችሁ የሚላቸው ኀጢአተኛ ነው አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገሥታትን ‘ምናምንቴ ናችሁ፣’ መኳንንትንም፣ ‘ክፉዎች ናችሁ’ የሚላቸው እርሱ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ፥ መኰንኖቹን፦ ክፉዎች ናችሁ ይላልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡን የማትጠቅም ነህ፤ መኳንንቱንም ክፉዎች ናችሁ፤ የሚላቸው ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ሰው ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ፥ መኳንንቱንም፦ ክፉዎች ናችሁ ይላልን? |
ጳውሎስም መልሶ፥ “አንተ የተለሰነ ግድግዳ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝዛለህን? እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት ይመታሃል” አለው።
ጳውሎስም፥ “ወንድሞች፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላውቅም መጽሐፍ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ አትናገር’ ይላልና” አላቸው።
ለሁሉም እንደሚገባው አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ስጡ፤ ዐሥራት ለሚገባው ዐሥራትን ስጡ፤ ሊፈሩት የሚገባውን ፍሩ፤ ክብር የሚገባውንም አክብሩ።