ኢዮብ 33:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግፍህን ተናግረሃል፥ የቃልህንም ድምፅ ሰምቻለሁ፥ እንዲህም ብለሃል፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በርግጥ የተናገርኸውን አድምጫለሁ፤ እንዲህም ስትል ሰምቻለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በጆሮዬ ተናግረሃል፥ የቃልህንም ድምፅ ሰምቻለሁ፤ እንዲህም ብለሃል፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእርግጥ እኔ የተናገርከውን ሁሉ ሳዳምጥ ቈይቼአለሁ፤ ከአንደበትህም የወጡትን ቃላት ሰምቼአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጆሮዬ ተናግረሃል፥ የቃልህንም ድምፅ ሰምቻለሁ፥ እንዲህም ብለሃል፦ |
ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
በእስራኤል ዘንድ ክፉ አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና። እኔም አውቃለሁ፤ ምስክርም ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ትፈልጋለህ ትመረምራለህም፤ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥