“ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፥ ነገሬንም አድምጥ።
“አሁን ግን ኢዮብ ሆይ፣ ንግግሬን ስማ፤ የምለውንም ሁሉ አድምጥ።
“እንግዲህ፥ ኢዮብ ሆይ፥ ንግግሬን እንድትሰማ፥ ቃሌንም ሁሉ እንድታደምጥ እለምንሃለሁ።
“አሁንም ኢዮብ ሆይ! የምነግርህን ስማኝ፤ የምልህንም ሁሉ በጥንቃቄ አድምጠኝ፤
ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ንግግሬን እንድትሰማ፥ ቃሌንም ሁሉ እንድታደምጥ እለምንሃለሁ።
ነገሬን ስሙ ስሙ፥ እኔ በጆሮአችሁ እነግራችኋለሁና።
“አሁን የአፌን ክርክር ስሙ፥ የከንፈሬንም ፍርድ አድምጡ።
ለሰው ፊት ማድላትን አላውቅም፤ ከሰውም የተነሣ የማፍረው ካለ ትሎች ይብሉኝ።
እነሆ፥ አፌን ከፍቻለሁ፥ አንደበቴም ይናገራል።
“እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሌን ስሙ፤ እናንተም ዐዋቂዎች፥ መልካም ነገርን አድምጡ።
የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፤” አለ።