በዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኀጢአትን እሠራለሁ?”
ኢዮብ 31:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ግርማ አስደንግጦኛልና፤ በእርሱም ከመያዝ በምክንያት ማምለጥ አልቻልሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ቍጣ በመፍራቴ፣ እንዲህ ያሉ ነገሮች መፈጸም አልቻልሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር መዓት አስደንግጦኛልና፥ በክብሩም ፊት ምንም ለማድረግ አልቻልሁም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን መቅሠፍት እፈራለሁ፤ ከግርማውም አስፈሪነት የተነሣ በፊቱ መቆም አልችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር መዓት አስደንግጦኛልና፥ በክብሩም ፊት ምንም ለማድረግ አልቻልሁም። |
በዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኀጢአትን እሠራለሁ?”
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
እግዚአብሔርን መፍራት ዐውቀን ሰዎችን እናሳምናለን፤ ለእግዚአብሔር ግን እኛ የተገለጥን ነን፤ እንዲሁም በልቡናችሁ የተገለጥን እንደ ሆን እንታመናለን።