የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት፦ ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ።
ኢዮብ 31:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱን ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ አባቱ ከእኔው ጋር አሳድጌው ነበር፤ ከእናቱም ማኅፀን ከተወለደ ጀምሮ አሳደግሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይልቁን ድኻ አደጉን ከታናሽነቴ ጀምሮ እንደ አባት አሳደግሁት፤ መበለቲቱንም ከተወለድሁ ጀምሮ መንገድ መራኋት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለነገሩማ ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባት ሆኜ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ መበለቲቱንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከወጣትነቴ ጀምሬ እንደ አባት ሆኜላቸዋለሁ፤ በሕይወቴ ዘመኔ ሁሉ ባልዋ የሞተባትን ረድቼአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱን ግን ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባቱ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ እርስዋንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፥ |
የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት፦ ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ።
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።