ኢዮብ 31:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወንድ ባሪያዬ ወይም ሴት ባሪያዬ በእኔ ዘንድ በተምዋገቱ ጊዜ፥ ፍርዳቸውን አዳልቼ እንደ ሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ፣ ፍርድ አዛብቼ ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወንዶችና ሴቶት አገልጋዮቼ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን ንቄ እንደሆነ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ አቅርበውልኝ አቤቱታቸውን ሳልቀበል ቀርቼ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድ ባሪያዬ ወይም ሴት ባሪያዬ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን ንቄ እንደ ሆነ፥ |
ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ ታወርሱአቸዋላችሁ፤ እነርሱም ለእናንተ ለዘለዓለም ውርስ ይሆናሉ፤ ነገር ግን ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤል ልጆች ማናቸውም ሰው ወንድሙን በሥራ አያስጨንቀው።
እናንተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣችሁን እያበረዳችሁ፥ በደላቸውንም ይቅር እያላችሁ፥ ትክክለኛውን አድርጉላቸው፤ ፊት አይቶ የማያዳላ ጌታ በእነርሱና በእናንተ ላይ በሰማይ እንደ አለ ታውቃላችሁና።
ጌቶች ሆይ፥ ለአገልጋዮቻችሁ ትክክለኛውን አድርጉላቸው፤ እውነትንም ፍረዱ፤ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና።