የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
ኢዮብ 31:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ፥ ድንግሊቱንም አልተመለከትሁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወደ ኰረዳዪቱ ላለመመልከት፣ ከዐይኔ ጋራ ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፥ እንግዲህ ቈንጆይቱን እንዴት በፍትወት እመለከታለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ቈንጆይቱን በፍትወት ዐይን እንዳልመለከት፥ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቼአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ እንግዲህስ ቈንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ? |
የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።