ኢዮብ 30:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሆዴ ፈላች፥ አላረፈችምም፤ የችግርም ዘመን መጣችብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውስጤ ያለው ነውጥ አላቋረጠም፤ የመከራ ዘመንም መጣብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንጀቴ ተናወጠ፥ አላረፈምም፥ የመከራም ዘመን መጣብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቤ ተጨነቀች፤ ምንም ሰላም አላገኘሁም፤ የመከራ ቀኖችም ደረሱብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንጀቴ ፈላች፥ አላረፈችም፥ የመከራም ዘመን መጣችብኝ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ማልደህ ተነሣ፤ በፈርዖንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
በእውነት ኤፍሬም ለእኔ የተወደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚያሰኝም ሕፃን ነው፤ በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አስበዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት፤ ርኅራኄም እራራለታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፤ ነፍሴም አእምሮዋን አጥታለች፤ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴም የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምታለችና ዝም እል ዘንድ አልችልም።
ሬስ። አቤቱ! ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፤ መራራ ኀዘን አዝኛለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመከነችኝ፤ በቤትም ሞት አለ።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።