ኢዮብ 30:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በጎ ነገርን በተጠባበቅኋት ጊዜ እነሆ ክፉ ቀኖች መጡብኝ፤ ብርሃንን ተስፋ አደረግሁ፥ ጨለማም መጣብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን መልካም ስጠብቅ፣ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ ብርሃንንም ስጠባበቅ፣ ጨለማ መጣብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በጎነትን ስጠባበቅ ክፉ ነገር መጣብኝ፥ ብርሃንን ተስፋ ሳደርግ ጨለማ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካም ነገር አገኛለሁ ብዬ ስመኝ፥ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ ብርሃን ይወጣልኛል ብዬ ስጠባበቅ፥ ቀኑ ጨለመብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በጎነትን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ ነገር መጣችብኝ፥ ብርሃንን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ ጨለማም መጣ። |
እኔም እንደምሸመግልና እንደማረጅ፥ እንደ ረዥም ዘንባባም ረዥም ዘመን እንደምኖር፥ እንደ አሸዋም ዘመኔን እንደማበዛ ዐሰብሁ።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
ስለዚህ ፍርድ ከእነርሱ ዘንድ ርቆአል፤ ጽድቅም አላገኛቸውም፤ ብርሃንን ሲጠባበቁ ብርሃናቸው ጨለማ ሆነባቸው፤ ብርሃንንም ሲጠባበቁ በጨለማ ሄዱ፤
በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ስለ ምን ተስፋ አደረግን? ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም፤ የፈውስን ጊዜ ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ድንጋጤ ሆነ።
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።