ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
ኢዮብ 30:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞት እንደሚያጠፋኝ አውቃለሁና ለሟችም ሁሉ ማደሪያው ምድር ናትና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሞት፥ ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ሁሉ ዕድል ፈንታ ለሆነው ለሞት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ ዐውቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሞት ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና። |
ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
ሞትን እንሞታለንና፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ እንሆናለንና፥ እግዚአብሔርም ነፍስን ይወስዳል። የተጣለውንም ከእርሱ ያርቅ ዘንድ ያስባል።
በምድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮቹም በአንተ ዘንድ የተቈጠሩ ናቸው፤ ዘመኑንም ወስነህ ትሰጠዋለህ፤ እርሱም ከዚያ አያልፍም።
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።
ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላቸውም።
“እኔም በምድር እንዳሉት ሰዎች ሁሉ ዛሬ ወደ መንገድ እሄዳለሁ፤ እናንተም አምላካችን እግዚአብሔር ስለ እኛ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ፥ በነፍሳችሁም ሁሉ ዕወቁ፤ ሁሉ ደርሶናል፤ ከእርሱም ያላገኘነው የለም።