ኢዮብ 30:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀዘን አኖርኸኝ፥ ከሕይወቴም አራቅኸኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤ በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስጋለብከኝ፥ በዐውሎ ነፋስ አቀለጥኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንሥተህ በነፋስ ላይ አስቀመጥከኝ፥ እንዲያዞረኝም አደረግህ፤ ዐውሎ ነፋሱም ያንገዋልለኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስቀመጥኸኝ፥ በዐውሎ ነፋስ አቀለጥኸኝ። |
ብዙዎች አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏፏቴ ውስጥ በኀይል እንደሚወርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮኻሉ፤ ያጠፉታልም፤ እነርሱም ከሩቅ ይወርዳሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፥ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው እንደ መንኰራኵር ትቢያም ይበተናሉ።
የእስራትህም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማዪቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጎራዴ ትመታለህ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ፤ እኔም በኋላቸው ጎራዴ እመዝዛለሁ።
ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋት እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፋስም ከዐውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከምድጃም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።