ኢዮብ 30:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረት የሌላቸው ሰዎች ደበደቡኝ፥ የገረፈችኝ እጅም በረታች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤ በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፥ በጠንካራ እጅህም አሰቃየኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ ጨከንክብኝ፤ በታላቅ ኀይልህም አሳደድከኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፥ በእጅህም ብረታት አስጨነቅኸኝ። |
ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።