ኢዮብ 30:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ እንደ ጭቃ ረገጠኝ፥ ዕድል ፋንታዬም አፈርና አመድ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤ እኔም ከዐፈርና ከዐመድ አልተሻልሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጭቃ ውስጥ ጣለኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ዐፈር ላይ ወርውሮ ስለ ጣለኝ፥ ትቢያና ዐመድ መስያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ በጭቃ ውስጥ ጣለኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ። |
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በግዞት ቤትም አደባባይ ወደ ነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።