ኢዮብ 30:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌሊት ሁሉ አጥንቶች በደዌ ይነድዳሉ፥ ጅማቶችም ይቀልጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደዌ በሌሊት ዐጥንቴን ይበሳል፤ የሚቈረጥመኝም ፋታ አይሰጠኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌሊቱ ስቃይ እስከ አጥንቶቼ ድረስ ይዘልቃል፥ ሁለመናዬንም ስለሚበላኝ ጅማቶቼ አያርፉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊቱን ሙሉ አጥንቶቼ በሕመም ይሠቃያሉ፤ ሕመሙም ዕረፍት አይሰጠኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌሊት አጥንቴ በደዌ ተነደለች፥ ጅማቶቼም አያርፉም። |
በተኛሁም ጊዜ፦ መቼ ይነጋል? እላለሁ፤ በተነሣሁም ጊዜ ዳግመኛ መቼ ይመሻል? እላለሁ፤ ከማታ እስከ ጥዋት ድረስ መከራን ጠገብሁ።
በዚያ ወራት እስኪነጋ ድረስ እንደ አንበሳ ታወክሁ፤ እንደዚሁም አጥንቶች ተቀጠቀጡብኝ፤ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ተጨነቅሁ።
እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።