ኢዮብ 30:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍለጋዬን አጠፋ፤ ልብሴን ገፈፈኝ፥ በቀስቱም ነደፈኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገድ ዘጉብኝ፤ የሚገታቸው ሳይኖር፣ ሊያጠፉኝ ተነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐዳናዬን ያበላሻሉ፥ ረዳት የሌላቸው ሰዎች መከራዬን ያበዛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መተላለፊያ መንገዴን ዘግተው ሊያጠፉኝ ይፈልጋሉ፤ ይህን ከማድረግ የሚገታቸው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጐዳናዬን ያበላሻሉ፥ ረዳት የሌላቸው ሰዎች መከራዬን ያበዛሉ። |
ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥዎቻችሁ ያስጨንቁአችኋል፤ አስጨናቂዎች ሴቶችም በላያችሁ ይሠለጥኑባችኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚያመሰግኑአችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጠፋሉ።