ኢዮብ 29:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያላኑም ከመናገር ዝም አሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ጫኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መኮንኖች ከመናገር ዝም ይሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲነጋገሩ የነበሩ የሕዝብ መሪዎችም እኔን ሲያዩ እጆቻቸውን በአፋቸው ላይ አድርገው ጸጥ ይሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹ ከመናገር ዝም አሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ጫኑ። |
“አንተ ስታስተምረኝ እኔ የምመልሰው ምን አለኝ? ይህንስ እየሰማሁ ከእግዚአብሔር ጋር እከራከር ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማኖር በቀር የምመልሰው ምንድን ነው?
እነርሱም፥ “ዝም በል፤ እጅህንም በአፍህ ላይ ጫን፤ ከእኛም ጋር ና፥ አባትና ካህንም ሁንልን፤ ለአንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእስራኤል ዘንድ ለነገድና ለወገን ካህን መሆን ማናቸው ይሻልሃል?” አሉት።