ኢዮብ 29:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራስጌዬ ላይ መብራቴ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለማውን ዐልፌ በብርሃኑ በሄድሁ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያን ጊዜ መብራቱ በራሴ ላይ ይበራ ነበር፤ በብርሃኑም በጨለማ ውስጥ ዐልፌ እሄድ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በራሴ ላይ መብራቱ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለማውን አልፌ በብርሃኑ በሄድሁ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያን ጊዜ በጨለማ ውስጥ ስሄድ፥ እግዚአብሔር መብራቱን እያበራልኝ በብርሃን እራመድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራሴ ላይ መብራቱ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለማውን አልፌ በብርሃኑ በሄድሁ ጊዜ፥ |
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፤ ብዙ አሕዛብንም ይዘልፋቸዋል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍን አያነሣም፤ ሰልፍንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።