እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ።
ኢዮብ 28:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል፤ በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር እንጀራን ታበቅላለች፥ ከበታቿ ያለው ግን እንደ እሳት ይገለባበጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር ለምግብ የሚሆን እህል ታበቅላለች። ውስጥዋ በእሳት ቀልጦ ይገለባበጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል፥ በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ።
በአፈር ምክንያት እንደሚከፈል ወንዝ የጽድቅን መንገድ የረሱ በኀጢአታቸው ይደክማሉ። ከሰዎችም መካከል ይለያሉ።