ኢዮብ 28:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰው ሁሉ ዘንድ ተረስታለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሰውራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕያዋን ፍጥረታት ዐይን ሁሉ ተሰውራለች፤ ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕያዋን ሁሉ ዐይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከሕያው ፍጡር ሁሉ የተሰወረች ናት፤ በሰማይ የሚበሩ ወፎች እንኳ ፈልገው አያገኙአትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕያዋን ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎች ተሸሽጋለች። |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።