ኢዮብ 28:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአፌር ወርቅም ጋር አትወዳደርም። በከበረ መረግድና በሰንፔር አትገመትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኦፊር ወርቅ፣ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ ኦፊር ከሚባል ወርቅና፥ መረግድና ሰንፔር ከሚባሉ ዕንቆች የከበረች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም። |
እጆቹ የተርሴስ ፈርጥ እንዳለባቸው እንደ ለዘቡ የወርቅ ቀለበቶች ናቸው፤ ሆዱ በሰንፔር ዕንቍ እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው፥
አንቺ የተቸገርሽ የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን የሚያበሩ አደርጋለሁ፤ መሠረትሽንም የሰንፔር አደርገዋለሁ።
ዛይ። ቅዱሳኖችዋ ከበረድ ይልቅ ነጡ፤ ከወተትም ይልቅ ነጡ፤ በመውጣታቸውም ሰንፔር ከሚባል ዕንቍ ይልቅ ፈጽመው ቀሉ።
በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያሰጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅም ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበትም ቀን ተዘጋጅተው ነበር።