ኢዮብ 28:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በእውነቱ ብር የሚወጣበት ቦታ አለ፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የብር ማዕድን የሚወጣበት፣ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእውነቱ ብር የሚወጣበት፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእውነቱ ማዕድን ተቈፍሮ ብር የሚወጣበትና ወርቅ የሚጣራበት ቦታ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነት ብር የሚወጣበት፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ። |
ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሰውዬው አንድ አንድ ወቄት የሚመዝን የወርቅ ጉትቻ፥ ለእጆችዋም ዐሥር ወቄት የሚመዝን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፤
ንጉሡም ሰሎሞን ያሠራው የመጠጫ ዕቃ ሁሉ ወርቅ ነበረ፤ ኵስኵስቱም የወርቅ ነበረ፤ የሊባኖስ ዱር የተባለውን የዚያን ቤት ዕቃ ሁሉ በወርቅ አስለበጠው። የብርም ዕቃ አልነበረም፤ በሰሎሞን ዘመን የብር ዋጋ ዝቅተኛ ነበርና።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።