ኢዮብ 27:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያቃጥል ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ያልፋል፤ ከቦታውም ይጠርገዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እርሱም አይገኝም፤ ከስፍራውም ይጠርገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምሥራቅ ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ይሄዳል፥ ከቦታውም ይጠርገዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምሥራቅ ነፋስ ከመኖሪያ ቤቱ ጠራርጎ ይወስደዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምሥራቅ ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ይሄዳል፥ ከቦታውም ይጠርገዋል። |
ከወንድሞቹ መካከል ይለያል፤ እግዚአብሔርም ከምድረ በዳ የሚያቃጥል ነፋስን ያመጣል፤ ሥሩን ያደርቃል፤ ምንጩንም ያነጥፋል፤ ምድርን ያደርቃል፤ የተወደዱ ዕቃዎችንም ሁሉ ያጠፋል።