መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ኢዮብ 27:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባለጠጋ ይተኛል፥ የሚያነቃውም የለም፤ ዐይኖቹን ይከፍታል፥ ይደነቃልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ዘለቄታ ግን የለውም፤ ዐይኑን በገለጠ ጊዜ ሀብቱ ሁሉ በቦታው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለ ጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው፥ ዓይኑን ሲከፍት፥ እርሱም የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው ለመጨረሻ ጊዜ ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ሲነቃ ግን ሀብቱ ሁሉ ጠፍቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ዳግመኛም አይተኛም፥ ዓይኑን ይከፍታል፥ እርሱም የለም። |
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። እንደ አመድማዶ በሙቀት ይጠወልጋል። ከቃርሚያው እንደሚወድቅ እሸትም ይቈረጣል።
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።