ለማትወልደው ለመካኒቱ በጎነትን አላደረገላትም፤ ለምትወልደውም አልራራም።
የማትወልደውን መካኒቱን ይቦጠቡጣሉ፤ ለመበለቲቱም አይራሩም።
“የማትወልደውን መካኒቱን ይበድላታል፥ ለመበለቲቱም መልካም አያደርግም።
ይህ ሁሉ የደረሰባቸው እነርሱ ልጆች የሌላቸው መኻኖች ሴቶችን በመበዝበዛቸውና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ምንም ርኅራኄ ባለማሳየታቸው ነው።
የማትወልደውን መካኒቱን ይበድላታል፥ ለመበለቲቱም በጎነት አያደርግም።
መበለቶችን ባዶአቸውን ሰድደሃቸዋል፥ ድሃአደጎችንም አስጨንቀሃቸዋል።
የድሃአደጎቹን አህያ ይነዳሉ የመበለቲቱንም በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ።
ለሞት የቀረበው መረቀኝ፤ የባልቴቲቱም አፍ ባረከኝ፤
እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤ የመበለቷን ወሰን ግን ያጸናል።