ኢዮብ 24:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠፋል። እንደ ሥራውም ይከፈለዋል። ዐመፀኛም ሁሉ እንደ በሰበሰ ዛፍ ይሰበራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተሸከመቻቸው ማሕፀን ትረሳቸዋለች፤ ትል ይቦጠቡጣቸዋል፤ ክፉዎች እንደ ዛፍ ይሰበራሉ፤ የሚያስታውሳቸውም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኅፀን ትረሳዋለች፥ ትልም በደስታ ይጠባዋል፥ ዳግመኛም የሚያስታውሰው የለም፥ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናቶቻቸው ሁሉ ይረሱአቸዋል፤ ሥጋቸውንም ትል ይበላዋል፤ ክፉ ሰዎች አይታወሱም፤ ነገር ግን እንደ ዛፍ ይሰባበራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅፀን ትረሳዋለች፥ ትልም በደስታ ይጠባዋል፥ ዳግመኛም አይታሰብም፥ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል። |
እንዲሁም ያንጊዜ ኃጥኣን ወደ ጽኑ መቃብር ሲገቡ አየሁ፥ ከቅድስት ስፍራም ወጥተው ተለዩ፤ እነርሱም በከተማዋ ተመሰገኑ፥ እንዲህ ሠርተዋልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
ነገር ግን ሙታን ሕይወትን አያዩአትም፤ ባለ መድኀኒቶችም አያስነሡም፤ ስለዚህም አንተ አምጥተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ ወንዶቻቸውንም ሁሉ አስወግደሃል።
“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም።