ኢዮብ 24:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአመንዝራም ዐይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፦ የማንም ዐይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አመንዝራ በዐይኑ ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤ ‘ማንም አያየኝም’ ብሎ ያስባል፤ ፊቱንም ይሸፍናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአመንዝራ ሰው ዐይን ጨለማን ይጠብቃል፦ የማንም ዐይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አመንዝራ ሰው የቀኑን መምሸት ይጠባበቃል፤ ማንም ሰው እንዳያየው ፊቱን ይሸፍናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፦ የማንም ዓይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል። |
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በስውር እያንዳንዱ በሥዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል ይላሉና” አለኝ።
እርሱም፥ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኀጢአት እጅግ በዝቶአል፤ ምድሪቱም በብዙ አሕዛብ እንደ ተመላች ከተማዪቱም እንዲሁ ዓመፅንና ርኵሰትን ተሞልታለች፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል፤ እግዚአብሔርም አያይም” ብለዋል።