ኢዮብ 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እኔ ስለ እርሱ ቸኰልሁ፤ በተገሠጽሁም ጊዜ አሰብሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህ ያሉ ብዙ ብያኔዎች እንዳሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ ያቀደውን ሁሉ ይፈጽመዋል፤ ይህንንም የሚመስሉ ብዙ ዕቅዶች አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔ ላይ የተወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህም ያለ ብዙ ነገር በእርሱ ዘንድ አለ። |
የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም።