ኢዮብ 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ትእዛዙ እወጣለሁ፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግሮቼ ርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሬ ዱካውን ተከትሎአል፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ከመስመር አልወጣሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮቼ እርሱ በሚወደው መንገድ ይሄዳሉ፤ በማወላወል ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግሬ ወደ እርምጃው ተጣብቆአል፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። |
በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።